Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሜሪካ ለታይዋን ተጨማሪ ሚሳኤሎችንና ሰው አልባ አውሮፕላን ለመሸጥ እቅድ እንዳላት ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካ ለታይዋን ተጨማሪ ሚሳኤሎችንና ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) የመሸጥ እቅድ እንዳላት አንድ ሪፖርት አመላከተ።
ቻይና ግዛቴ በምትላት ታይዋን ላይ እያሳደረች ያለውን ጫና ተከትሎ አሜሪካ ተጨማሪ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን ለታይዋን ለመሸጥ ማቀዷን ከነጩ ቤተ መንግስት የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።
በዚህም የትራምፕ አስተዳደር ኤም ኬ9 ድሮኖች እና ዘመናዊ ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ለታይዋን ለመሸጥ ማቀዷ ነው የተሰማው።
የሽያጩ መጠንም ወደ 5 ቢሊየን ዶላር እንደሚጠጋም ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት።
ቻይና አሜሪካ ለታይዋን ምንም አይነት መሳሪያ እንዳትሸጥ ስታሳስብ መቆየቷ ይታወሳል።
ነገር ግን የትራምፕ አስተዳደር በቻይና ላይ ጫና ለማሳደር እየሞከረ ይገኛል።
ምንጭ፡-አልጀዚራ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
Exit mobile version