Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ልደቱ ህገመንግስቱን ለመናድ በማሰብ የተለያዩ ህገመንግስቱን የሚቃረኑ የሽግግር ሰነዶችን በማዘጋጀት በቀረበባቸው 2ኛ ክስ ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ልደቱ አያሌው ህገመንግስቱን ለመናድ በማሰብ የተለያዩ ህገመንግስቱን የሚቃረኑ የሽግግር ሰነዶችን አዘጋጅተዋል ተብለው በቀረበባቸው 2ኛ ክስ ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ።

በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ችሎት ዛሬ የአቶ ልደቱ አራት ጠበቆች ተገኝተዋል።

ዛሬ ችሎቱ ይህን 2ኛ ክስ በችሎት በንባብ ለማሰማት በሰጠው ቀጠሮ መሰረት የተሰየመ ቢሆንም ዐቃቤ ህግ በማስረጃነት ለፍርድ ቤቱ የያዘውን ሲዲ ከክሱ ጋር ለተከሳሽ ባለመስጠቱ ምክንያት ነው ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጠው።

በዚህም የተከሳሽ ጠበቆች ሲዲው ደርሶን ተመልክተን እና ተዘጋጅተን እንቅረብ ሲሉ ያቀረቡትን ጥያቄ የተቀበለው ፍርድ ቤቱ ሲዲው ደርሷቸው ተዘጋጅው ክሱን በችሎት ለማንበብ ለጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በታሪክ አዱኛ

Exit mobile version