Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አየር መንገዱ የበረሃ አንበጣን ለመከላከል የሚያገለግሉ ሄሊኮፕተሮችን እየገጣጠ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረሃ አንበጣን ለመከላከል ከውጭ የመጡ ሄሊኮፕተሮችን እየገጣጠ ነው፡፡

አየር መንገዱ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለበረሀ አንበጣ ማጥፊያነት ኬሚካል ርጭት የሚያገለግሉ ሶስት ሄሊኮፕተሮችን ማጓጓዙ ታውቋል፡፡

ሄሊኮፕተሮቹ ከውጭ በመጡ ባለሙያዎች እና በአየር መንገዱ የአውሮፕላን ጥገና ባለሙያዎች በአየር መንገዱ የጥገና ማዕከል ውስጥ እየተገጣጠሙ እንደሚገኙ ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version