Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዳማ ከተማ ህንጻ ተደርምሶ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ከተማ ህንጻ ተደርምሶ ባደረሰው አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
የከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ለኢዜአ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው በከተማው ደምበላ ክፍለ ከተማ ኢሬቻ ቀበሌ ውስጥ ነው።

በቀበሌው ልዩ ስሙ ኮሎኔል ደጀኔ ስሜ ትምህርት ቤት አቅራቢያ ያለው ሃዊ ሆቴል በመደርመሱ አደጋው መድረሱንም ተናግረዋል።

ሆቴሉን በአዲስ ህንፃ ለመተካት አሮጌውን እያፈረሱ ባሉት የቀን ሠራተኞች ላይ በደረሰው አደጋ ከመካከላቸው የአራት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉንም አስታውቀዋል።

ሁለት ሰዎች ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በአዳማ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
የአደጋው መንስኤ የጥንቃቄ ጉድለት መሆኑንም አመላክተዋል።

Exit mobile version