Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸውም ለጤና ዘላቂ የልማት ግቦች እና ለኮሮና ቫይረስ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ፕሮጀክት በዓለም ባንክ በኩል የሚደረገውን የፋይናንስ ድጋፍ ተፈጻሚነት ማፋጠን በሚቻልበት ዙሪያ መክረዋል።
በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የጤና ሴክተር ሽግግርን ለመደገፍ ስራዎች ሊሰሩባቸው በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያም ምክክር ማድረጋቸው በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ያወጣው መረጃ አመልክቷል።
Exit mobile version