Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሰዓድ ሃሪሪ በድጋሚ የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከዓመት በፊት ስልጣን የለቀቁት የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰዓድ ሃሪሪ በድጋሚ መመረጣቸው ተሰማ፡፡

ሃሪሪ በፓርላማ ድጋፍ የተነፈጋቸውን ሙስጠፋ አዲብን በመተካት ነው በድጋሚ ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት፡፡

ሃሪሪ በፓርላማ ውስጥ መንግስት ለመመስረት የሚያበቃ ድጋፍ ማግኘታቸው ተነግሯል፡፡

ሊባኖስ በአሁኑ ወቅት ከእርስ በርስ ጦርነት በኋላ የገጠማትን ቀውስ ለመፍታት ጥረት ላይ ነች ተብሏል፡፡

በድጋሚ ወደ ስልጣን የመጡት ሃሪሪም ፈተና እንደሚጠብቃቸው ነው የተሰማው፡፡

የሱኒው መሪ ሰዓድ ሃሪሪ የዛሬ ዓመት ነበር በሃገሪቱ የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎ ስልጣን የለቀቁት፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

Exit mobile version