Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ህብረተሰቡ 14 የሚሆኑ የለውዝ ቅቤ ምርቶችን እንዳይጠቀም ባለስልጣኑ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህብረተሰቡ ከፍተኛ የሆነ የአፍላ ቶክሲን (Aflatoxine) የተገኘባቸውን 14 የለውዝ ቅቤ ምርቶችን እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ ባደረገው ቁጥጥርና ፍተሻ አማካኝነት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ምርቶቹ ከፍተኛ አፍላ ቶክሲን (Aflatoxine)እንደተገኘባቸው ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ለውዞቹን የሚያመርቱ ተቋማትም ላይ የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ አምራቾቹን ለማግኘት አለመቻሉንም አስታውቋል፡፡
የሚመለከተቻው የቁጥጥር አካላት ምርቶቹ ከገበያ ላይ በመሰብሰብ እንዲያስወግዱ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡
ባለስልጣኑ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ያገዳቸው የለውዝ ቅቤዎች፡-
ምስራቅ የለውዝ ቅቤ
ሳራ የለውዝ ቅቤ
ዳና የለውዝ ቅቤ
ሰገን የኦቾሎኒ ቅቤ
አርሂቡ የለውዝ ቅቤ
ረጃት የለውዝ ቅቤ
ኢትዮ የለውዝ ቂቤ
ጽዮን የለውዝ ቅቤ
ማሀሩን የኦቾሎኒ ቅቤ
ላቪሊ የሎዝ ቂቤ
እናት የሎዝ ቅቤ
ኤ.ኤፍ የሎዝ ቅቤ
መና የኦቾሎኒ ቅቤ
ሂር የለውዝ ቅቤ ናቸው፡፡
Exit mobile version