Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በታንዛኒያ ጠቅላላ ምርጫ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛኒያ ጠቅላላ ምርጫ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ቀጣይ የሃገሪቱን መሪ ለሚወስነው ምርጫም የሃገሬው ዜጎች ድምጽ መስጠት ጀምረዋል፡፡

የምርጫው ውጤት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

ሃገሪቱን ከነጻነት በኋላ እያስተዳደራት ያለው የሲ ሲ ኤም ፓርቲ ሊቀ መንበርና የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ለሁለተኛ ጊዜ በስልጣን መቆየት እንደሚፈልጉ ተገልጿል፡፡

ዋና ተፎካካሪያቸው የተቀናቃኝ ፓርቲ መሪው ቱንዱ ሊሱ ናቸው፡፡

በምርጫው የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በርናርድ ሜምቤን ጨምሮ 15 ዕጩዎች ይወዳደራሉ፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

Exit mobile version