Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በክልሉ በእርሻ ኢንቨስትመንት ተሠማርተው ያላለሙ የ29 ባለሀብቶች ፈቃድ ተሠረዘ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በእርሻ ኢንቨስትመንት ተሠማርተው ያላለሙ የ29 ባለሀብቶችን ፈቃድ መሰረዙን የክልሉ የኢንቨስትመንት ቦርድ ገለፀ።
የኢንቨስትመንት ቦርዱ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ በእርሻ ኢንቨስትመንት ተሠማርተው ወደ ልማት ያልገቡ የ29 ባለሀብቶችን ፍቃድ ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ ውሳኔ አስተላልፏል።
ፈቃዳቸው የተሠረዘው ባለሃብቶች በክልሉ በእርሻው ኢንቨስትመንት ለመሠማራት በወሠዱት ፈቃድ መሠረት መሬቱን ያላለሙ መሆኑን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ባለሃብቶቹ በገቡት ውል መሠረት እንዲያለሙ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ማልማት ባለመቻላቸው ፈቃዳቸው መሠረዙንም ቦርዱ አስታውቋል።
Exit mobile version