Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሩጫ እና ብስክሌት ቅብብል ውድድር በእንጦጦ ፓርክ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሩጫ እና ብስክሌት ቅብብል ውድድር በእንጦጦ ፓርክ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

ውድድሩ በቀጣዩ ወር መግቢያ ይደረጋል ነው የተባለው።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው ውድድር በአንድ ቡድን አራት ሰዎች እንደሚካፈሉበት ይጠበቃል።

ከአራቱ ሰዎች ሁለቱ ብስክሌተኞች፣ቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ ሯጮች እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ብስክሌተኞቹ ስምንት ኪሎ ሜትር ሯጮች ደግሞ ሁለት ኪሎ ሜትር ርቀት ይሸፍናሉ ተብሏል።

በውድድሩ ለመሳተፍ 30 ቡድኖች ተመዝግበው 120 ሰዎች እንደሚካፈሉበት ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ውድድሩን ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ኮካ ኮላና ከኩሪፍቱ አድቬንቸር መሆናቸው ነው የተገለጸው።

Exit mobile version