Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሎዛ አበራ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ፈረመች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሎዛ አበራ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ፈረመች፡፡

የቡድኑ አሰልጣኝ አቶ ብርሀኑ ግዛው ለረጅም ጊዜ ሲከታተሏት እንነበር ገልጸው ተጫዋቿ ቡድናቸውን በመቀለቀሏ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ሎዛ አበራ በበኩሏ ቡድኑን በመቀላቀሏ መደሰቷንና ከሌሎች የቡድን አጋሮቿ ጋር በመሆን ውጤታማ ለመሆን እንደምትሠራ ገልፃለች፡፡

ሎዛ ባለፈው ዓመት ለማልታው ቢርኪርካራ የሴቶች እግር ኳስ ክለብ በመሰለፍ በኮኮብ ተጫዋችነት እና ኮኮብ ግብ አግቢነት አጠናቃለች፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማህበር አቶ አሊ አህመድ የባንኩ የሴቶች ስፖርት ክለብ ውጤታማ እንደነበር መግለጻቸውን ከባንኩ የፌስቡክ ገጽ ላይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ውጤቱንም በላቀ ሁኔታ በማስቀጠል የ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ለመሆን እና በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ለመጀመሪያ ጊዜ ለመሳተፍ ማለማቸውን ነው የገለጹት፡፡

Exit mobile version