Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሩሲያ፣ ቻይና እና ኢራን የጋራ የባህር ሃይል ልምምድ ጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ፣ ቻይና እና ኢራን የጋራ የባህር ሃይል ልምምድ ጀመሩ።

ለአራት ቀናት ይቆያል የተባለው ልምምድ በህንድ ውቅያኖስ እና የኦማን የባህር ሰርጥ ላይ ነው እየተካሄደ ያለው።

የሩሲያ የባህር ሃይል ልምምዱን የተቀላቀለ ሲሆን፥ ቻይና በዛሬው እለት የባህር ሃይሏን ወደ ስፍራው ትልካለች።

ቴህራ ልምምዱ ለሰላም፣ ወዳጅነትና በአካባቢው በትብብር ደህንነትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን ገልጻለች።

የቻይናው መከላከያ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ው ቂያን በበኩላቸው፥ ልምምዱ የሶስቱን ሃገራት ትብብርና ወዳጅነት እንደሚያጠናክር ተናግረዋል።

ልምምዱ በባህር ዘራፊዎች በመርከቦች ላይ የሚቃጣን ጥቃት መከላከል በሚቻልበት አግባብ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

የኢራን ብሄራዊ አብዮታዊ ዘብም በልምምዱ ተካፋይ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

Exit mobile version