Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሙስና የተማረረው ግብፃዊ ታህሪር አደባባይ ላይ እራሱን በእሳት አቃጠለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድ ግብፃዊ ግለሰብ ካይሮ በሚገኘው ታህሪር አደባባይ ላይ እራሱን በእሳት ማቃጠሉ ተነገረ።
ግለሰቡ አሁን ላይ በካይሮ በሚገኝ ሆስፒታል የህምና ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝም ነው ሬውተርስ በዘገባው ያሰፈረው።
ክስተቱን በተመለከተ እስከአሁን ድረስ ከመንግስት ባለስልጣናት የተሰጠ አስተያየት የለም።
በማህበራዊ ሚዲያዎች የተዘዋወረው ተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚያሳየው እራሱን በእሳት ያያዘው ግለሰብ በሀገሪቱ ባለው ሙስና መማረሩን ሲግልፅ ነበር ተብሏል።
ግለሰቡ እራሱን በእሳት ከማቃጠሉ በፊት ከፍ ያለ ድምፅ እያሰማ ያለቅስ እንደነበርም ዘገባው አስፍሯል።
Exit mobile version