Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያና የኒጀር የመልስ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲካሄድ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ እና የኒጀር የመልስ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም በዝግ እንዲካሄድ መወሰኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

የመልስ ጨዋታው በባሕር ዳር ስታዲየም ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት እንደነበር ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም ኢትዮጵያ ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲካሄድ ለአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ጥያቄ አቅርባ ነበር።

ካፍም ጥያቄውን ተቀብሎ ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታድየም በዝግ እንዲካሄድ ውሳኔ አስተላልፏል።

ኒጀር ላይ በተደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ኒጀር 1 ለ 0 ማሸነፏ የሚታወስ ነው።

Exit mobile version