Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ እና ፊንላንድ ከ824 ሚሊየን ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ እና ፊንላንድ ከ 824 ሚሊየን ብር በላይ የድጋፍ ስምምነት በዛሬው ዕለት መፈራረማቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ድጋፉ ለአራተኛው ዙር ማህበረሰብ አቀፍ የንፁህ ውሃ እና ንፅህና አቅርቦት እንደሚውል ነው የተነገረው።

ፕሮግራሙ የማህበረሰብ ጤናን፣ ማህበራዊ ልማትን ለማሻሻል እና  ድጋፍ ፈሰስ በሚደረግበት አከባቢ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ለሚያስችል ስራ ይውላል ነው የተባለው።

ድጋፉ በኦሮሚያ፣ አማራ ፣ ደቡብ ፣ ትግራይ ፣ሲዳማ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የሚውል መሆኑ ተጠቁሟል።

ድጋፉን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሪት ያስሚን ዎሃብረቢ እና በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ኦቲ ሆሎፓይኔን ተፈራርመዋል።

 

Exit mobile version