Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በከፍተኛ ባለስልጣናት ጥበቃና እጀባ ያሰለጠናቸውን 113 ፖሊሶች አስመረቀ

የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በሁርሶ የመከላከያ ሠራዊት ማሰልጠኛ ማዕከል ለመጀመሪያ ግዜ በከፍተኛ ባለስልጣናት ጥበቃና እጀባ ያሰለጠናቸውን 113 ፖሊሶች አስመረቀ።
የምረቃ ስነ ስርዓቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ እና የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወይዘሮ አዲስአለም በዛብህ በተገኙበት መከናወኑን የሰላምና ጸጥታ ጉዳት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዚህ ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር እና የሰላምና ጸጥታ ጉዳት ቢሮ ሀላፊ አቶ ናስር ዩያ የእንካን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዕለቱ በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ከእለቱ የክቡር እንግዶች የተዘጋጀላቸውን ሽልማትና ሰርተፍኬት ተቀብለዋል።
Exit mobile version