Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሎዛ አበራ የቢቢሲ 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ውስጥ ተካታለች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሎዛ አበራ ዓለም ላይ በቢሲ ከተመረጡ 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች መካከል አንዷሆና ተመርጣለች፡፡

ቢቢሲ በዚህ አመት ለውጥን የሚመሩ እና ለውጥ የሚያመጡ 100 ሴቶችን በዓለም ዙሪያ የመረጠ ሲሆን ሎዛ አበራ በስፖርቱ ዘርፍ ከ100ዎቹ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች አንዷ ሆናለች፡፡

ቢቢሲ በዕውቀት፣ በአመራርነት፣ በፈጠራ እና በማንነት ዘርፎች ውስጥ ተጽዕኖ ፈጥረዋል ያላቸውን ሴቶች ስም ዝርዝር ያወጣ ሲሆን ኢትዮጵያዊቷ የእግር ኳስ ተጫዋች ሎዛ አበራ ተካታለች፡፡

ሎዛ አበራ ከአሁን በፊት የተለያዩ እውቅናዎች እና ሽልማቶችን ማግኘቷ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

Exit mobile version