Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በምስራቅ ጉጂ ዞን 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጂ ዞን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

እንደ ክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፃ የሽብር ቡድኑ ላይ እርምጃው የተወሰደው በዞኑ ጎሮ ዶላ ወረዳ ለጥፋት ሲንቀሳቀሱ ነው፡፡

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሰላም ማስከበር የስራ ሂደት ኃላፊ ዋና ሳጅን ጉተማ ሳፈዮ ቡድኑ በአካባቢው እየተዘዋወረ ጉዳት እንዳያደርስ በንቃት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከጥፋት ቡድኑ አራት ክላሽ፣ አንድ ኤም-16፣ አንድ የእጅ ቦምብና አራት ትጥቅ ተይዟልም ነው ያሉት፡፡

የክልሉ ልዩ ኃይል፣ መደበኛ ፖሊስና ሚሊሻ ፀረ ሰላም ኃይሎቹን ለመደምሰስ እና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version