Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባውን ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ያካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ነገ ያካሄዳል፡፡
በእለቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በወቅታዊ የሃገሪቱ ጉዳዮች ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እንዲሁም የምክር ቤቱን 6ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ ሌላኛው የእለቱ አጀንዳ መሆኑን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version