Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በዳንሻ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዳንሻ ከተማ ህዝባዊ የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ፡፡

በሰልፉ ላይ ህዝቡ የህወሓት ጁንታን በማውገዝ መልዕክቶችን አስተላልፏል፡፡

ከዳንሻ ከተማና አካባቢዋ የተውጣጡ ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምስጋና በማቅረብ በሚደረገው ህግ የማስከበር ዘመቻ ከጎናቸው መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ጁንታውን ላስወገደው መከላከያ ሰራዊት እና ለአማራ ህዝባዊ ሃይል ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም ሰልፈኞቹ በአካባቢው የሚገኙ የጁንታው አባላት ትጥቅ እንዲፈቱና የማይካድራውን ጭፍጨፋ የፈጸሙ አካላት በጦር ወንጀል ይጠየቁልን ማለታቸውን ከአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version