Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአዲስ አበባ አትክልት ተራ በአዲሱ የገበያ ማዕከል ከነገ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ አትክልት ተራ በአዲሱ የገበያ ማዕከል ከነገ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በሰጡት መግለጫ ጃንሜዳ የሚገኘው ጊዜያዊ አትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ የገበያ ስፍራ የከተማው አስተዳደር ባዘጋጀው የገበያ ማዕከል እንዲዘዋወሩ በተወሰነው መሰረት የዕጣ ማውጣት ስርዓቱ ተጠናቆ ውል መዋዋል ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ተጠናቆ ከነገ ጀምሮ ጃንሜዳ የነበረው አትክልት ተራ ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ በተገነባው የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ ገበያ ማዕከል ተዘዋውሮ ስራ የሚጀምር መሆኑን ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

Exit mobile version