Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመኖሪያ ቤቱ ፈንጅና ቦምብ የተገኘበት የጎሚስታ ሰራተኛ ፍርድ ቤት ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመኖሪያ ቤቱ ፈንጅና ቦምብ ተገኝቶበታል የተባለውና ገብረመስቀል ወልደምህረት የተሰኘው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡

ግለሰቡ በዛሬው ዕለት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ሁለተኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የተጠርጣሪውን ጉዳይ ተመልክቷል፡፡

መርማሪ ፖሊስ ባደረኩት ምርመራ ተጠርጣሪው በማህበራዊ ድረ-ገጽ ላይ ‘‘የፌደራል መንግስት መቀጠል የለበትም’’ በሚል ቅስቀሳ ሲያደርግ እንደነበር በማስረጃ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

ከህወሓት ጸረ-ሰላም ቡድን ተልዕኮ ተቀብሎ ሲንቀሳቀስ ነበር ያለው መርማሪ ፖሊስ በመኖሪያ ቤቱ ባደረገው ብርበራ ፈንጅና ቦምቦች ማግኘቱን አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ለሚያደርገው ተጨማሪ ምርመራ 14 ቀን እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡

ተጠርጣሪው በበኩሉ 20 ዓመት አዲስ አበባ መኖሩን በመጥቀስ በመኖሪያ ቤቱ መሳሪያ መገኘቱን እንደሚያምንና ሌላ የወንጀል ተሳትፎ እንደሌለው በማስረዳት ተከራክሯል፡፡

ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በታሪክ አዱኛ

Exit mobile version