Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፕሪምየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ መቐለ 70 እንደርታን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዛሬ በተካሄደው 6 ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ  መቐለ 70 እንደርታን አሸንፏል።

መቐለ 70 እንደርታን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ  2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የቅዱስ ጊርጊስን የማሸነፊያ ግቦች ሳላህዲን ሰዒድ እና አቤል ያለው ሲያስቆጥሩ፥ አሸናፊ ሀፍቱ ደግሞ በጨዋታው መጠናቀቂያ ላይ ለመቐለ 70 እንደርታ ብቸኛዋን ጎል አስቆጥሯል።

ይህን ተከትሎም  ቅዱስ ጊዮርጊስ  የውድድር ዓመቱን 3ኛ ድል ማስመዘገብ ችሏል።

 

Exit mobile version