Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመተከል ዞን የተቋቋመው ግብረ ሀይል ከመተከል ዞን የሀገር ሽማግሌዎች እና የህብረተሰቡ ተወካዮች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ሃይል ከመተከል ዞን የሀገር ሽማግሌዎች እና የህብረተሰቡ ተወካዮች ጋር ተወያየ ፡፡

የግብረ ሃይሉ ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ የከሰረው የህውሓት ጁንታ ቡድን ኢትዮጵያን የማዳከም ተልዕኮ እኩይ ቡድኖችን በማደራጀት  በመተከል ዞን በጅምላ ጥቃት መፈፀሙን አስታውሰው።

የጥቃቱ ዋነኛ ኢላማ የግድቡን ግንባታ ማስተጓጎልና ከተቻለም ማስቆም ነው ያሉት ሰብሳቢው ይህም ምኞት እንጂ በተግባር የሚሞከር አይደለም ብለዋል ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራ እና ተከብራ ትኖራለች ብለዋል ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በበኩላቸው ብሔርን ከብሔር በማጋጨት በሃገሪቱ  ውስጥ የማያባራ የእርስ በእርስ ጦርነት ለመክፈት ምኞት የነበረው የህወሃት የህልም ቅዠት ሆኖ ቀርቷል ነው ያሉት።

የሀገር ሽማግሎዎች እና የህብረተሰቡ ተወካዮች በሰጡት አስተያየት መቼም ቢሆን ህዝብ ለህዝብ ጠላት ሆኖ አያቅም

ሲሉ መግለፃቸውን ከሰራዊቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እኛም ለረጅም አመታት አብረት የኖርን ህዝቦች ነን ፤ የእሱ ተላላኪዎች የሆኑትን ለማጥፋት በሚደረገው ወታደራዊ ዘመቻ ከሠራዊቱ ጎን እንቆማለን ሲሉ ተናግረዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version