Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ይበልጣል በሱዳን ከኖርዌይ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን የኖርዌይ አምባሳደር ቴሬዝ ሎክን ህዜል ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደሩ ከአምባሳደር ቴሬዝ ሎክን ህዜል ጋር በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይን በተመለከተ ውይይት አድርገዋል።

ከዚህ ጋር በተያይዘ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትን፣ የሰብዓዊ መብት አያያዝን እንዲሁም የኢትዮጵያንና የሱዳንን ድንበር እና በቀጠናው የሚስተዋሉ ጉዳዮችን በተመለከተ አምባሳደሯ ላነሷቸው ጥያቄዎች ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በዚሁ መሰረት በትግራይ ክልል ከሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትና ሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር በተያያዘ የሚነሱ የተዛቡ አስተያየቶች መንግስት በአካባቢው ያለውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በሚያደርገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ በመሆናቸው ለትግራይ ሕዝብም ሆነ በአጠቃለይ ለኢትዮጵያዊያን እቆረቆራለሁ የሚል አካል ካለ የመንግስትን ጥረት መደገፍ እንደሚገባ አምባሳደር ይበልጣል አስረድተዋል፡፡

አምባሳደሩ በማያያዝም የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ችግር የሚፈቱባቸው መንገዶች በግልፅ በስምምነት የተቀመጡ በመሆኑ በዚሁ መሰረት ዘላቂ ሰላም በሁለቱ ሀገራት እና በቀጠናው በሚያመጣ መልኩ መፍታት እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ከሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version