Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የከተራ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከተራ በዓል በዛሬው ዕለት በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በመከበር ላይ ይገኛል።
በመላ ሀገሪቱ ታቦታት ከአድባራት ወጥተው በካህናት፣ በዲያቆናት እና በምዕመናን ታጅበው ወደ ጥምቀተ ባህሩ በመውረድ ላይ ይገኛሉ።
ታቦታት ወደ ማደሪያቸው ጥምቀተ ባህር ከደረሱ በኋላም አዳራቸውን በዚያው የሚያደርጉ ሲሆን፥ በካህናትና ዲያቆናት ዝማሬና ሌሎች ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ይከወናሉ።
ነገ በማግስቱ ደግሞ የጥምቀት በዓል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች የሚከበር ይሆናል።
በዓሉ በአዲስ አበባ በጃን ሜዳ በአቅራቢያ የሚገኙ ደብራትና ገዳማት ታቦታት የጥምቀት በዓልን በጋራ የሚያከብሩ ሲሆን፥ ዛሬ ከአድባራትና ገዳማት ጉዞ በመጀመር ታቦታቱ ምሽት ላይ ጃን ሜዳ የሚያድሩ ይሆናል።
በአዲስ አበባ ካሉ የታቦታት ማደሪያ መካከል አንዱ በሆነው ወደ ጃንሜዳ ታቦታት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎችና ሠራተኞች፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ በበርካታ ካህናት፣ ምዕመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ታጅበው ተጉዘዋል።
የከተራና የጥምቀት በዓላት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ ሃይማኖታዊና የአደባባይ በዓላት መካከል ይጠቀሳሉ።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version