Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢፌዴሪ አየር ኃይል የኤር ሎጅስቲክስ በህግ ማስከበር ዘመቻው ኃላፊነታቸውን ለተወጡ እና ለተቋማዊ የለውጥ ጉዞ የድርሻቸውን ላበረከቱ የሰራዊቱ አመራሮችና አባላት እውቅና ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 15 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢፌዴሪ አየር ኃይል የኤር ሎጅስቲክስ በህግ ማስከበር ዘመቻ ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ እና ለተቋማዊ የለውጥ ጉዞ ስኬታማነት የድርሻቸውን ላበረከቱ የሰራዊቱ አመራሮችና አባላት እውቅና ሰጠ ::

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ “ይሆናል ብለን ፍጹም ባላሰብንበት ሁኔታ ከሃዲው የህወሓት ጁንታ ጥቃት ቢፈጽምብንም አየር ኃይላችን በተለመደ ህዝባዊ ጀግንነቱ የጽንፈኛውን አከርካሪ በመስበር በአጭር ጊዜ ውስጥ ታላቅ ድል አስመዝግቧል” ብለዋል፡፡

ለተቋሙ ወሳኝ የድል ጉዞ የሁሉም አየር ኃይል ክፍሎች የተቀናጀ ጥምረትና የጋራ ድምር ውጤት መሆኑን ያወሱት ዋና አዛዡ በተለይም የኤር ሎጂስቲክስ ያበረከተው ጉልህ አስተዋጽኦ ትልቅ ምስጋናና ክብር የሚያሰጥ አኩሪ ተግባር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የኢፌዴሪ ምክትል አዛዥ ለኤር ሎጅስቲክስ ብርጋዴር ጄኔራል ነገራ ሌሊሳ በበኩላቸው ኤር ሎጅስቲክስ ከዚህ በበለጠ ወትሮ ዝግጁነት ውጤታማነቱን በማረጋገጥ ለተቋሙ የለውጥ ስኬት ተልእኮውን በትጋት እንደሚወጣ ገልጸዋል፡፡

በኢፌዴሪ አየር ኃይል ከአራቱ ምክትሎች አንዱ የሆነው ምክትል አዛዥ ለኤር ሎጀስቲክስ ፣ የምድር ድጋፍ ሰጪ ተሽከርካሪዎችን፣ የአቪየሽን ድጋፍ ሰጪ መሳሪያዎችን ኤሌክትሪካልና ኤሌክትሮኒክስ ሬዲዮ ጥገናዎችን በማከናወንና በሌሎችም ዘርፎች የድርሻውን እየተወጣ የሚገኝ ክፍል እንደሆነ መጠቀሱን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version