Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኡበርና ሃዩንዳይ በራሪ ታክሲዎችን በጋራ ሊሰሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2012 (ኤፍቢሲ) ኡበርና ሃዩንዳይ በራሪ ታክሲዎችን በጋራ ሊሰሩ መሆኑን አስታወቁ።

ሁሉቱ ኩባንያዎች አዲስ የሚሰሩትን በራሪ ተሽከርካሪ በላስ ቬጋሱ የንግድ ትርኢት ይዘው እንደሚቀርቡ አስታውቀዋል።

አራት ተሳፋሪዎችን የሚይዘው በራሪ ታክሲ በሰዓት እስከ 320 ኪሎ ሜትር መጓዝ እንደሚችል ተገልጿል።

ሁለቱ ኩባንያዎች በዚህ ሳምንት በላስ ቬጋስ በሚደረገው የንግድ ትርኢት ላይ የታክሲ አገልግሎት ይሰጣል ያሉትን በራሪ ተሽከርካሪ ሞዴል ይፋ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።

ኡበር በፈረንጆቹ 2023 ለደንበኞቹ የበራሪ ታክሲ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ነው የገለጸው።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

Exit mobile version