Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፕሪምየር ሊጉ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መሪነቱን ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተካሂደዋል።

ሁለተኛ ደረጃ ላይ የነበረው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ወደ ድሬዳዋ በማቅናት 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል፡፡

በሌላ ጨዋታ መሪው ፋሲል ከነማ ወደ ሶዶ በማቅናት ከወላይታ ዲቻ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 1 በማጠናቀቁ ቢጫ ለባሾቹ ፕሪምየር ሊጉን በ14 ነጥብ መምራት ጀምረዋል፡፡

ሶስተኛ ደረጃ ላይ የነበረው መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው አዳማ ከተማን በማስተናገድ 2 ለ 0 አሸንፏል።

ውጤቱን ተከትሎም በ13 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ባህርዳር ላይ ኢትዮጵያ ቡናን ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በሌላ ጨዋታ በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ የነበረው ሀድያ ሆሳዕና በሜዳው ሲዳማ ቡናን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ጅማ አባ ጅፋር ወልቂጤ ከተማን 1 ለ 0 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሽሏል።

ሀዋሳ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

Exit mobile version