Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአውሮፓ  ህብረት በአፍሪካ የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽ ለማድረግ 100 ሚሊየን ዩሮ መደበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የአውሮፓ ሕብረት በአፍሪካ የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽ ለማድረግ  100 ሚሊየን ዩሮ መመደቡን አስታውቋል፡፡

በአህጉሪቱ የኮቪድ-19ን ጨምሮ ሌሎች በሽታዎችን ለመከላከል የሚውሉ ክትባቶችን በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ 100 ሚሊየን ዩሮ መድቦ እየሰራ  መሆኑንየኮሚሽን ፕሬዚዳንት በትዊተር ገጻቸው መልእክጽ አስተላልፈዋል፡፡

የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንት ቮን ደር ሌይን  በመልዕክታቸውም በአፍሪካ ክትባቱን የሚያመርቱ ኩባንያዎችን አቅም ለማጎልበት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

በዚህም የኮቪድ-19 ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ወደፊት ለሚከሰቱ ወረርሽኞች ክትባት ለማዘጋጀት አቅም ይፈጥራልም ነው ያሉት፡፡

ድጋፉ በአፍሪካ የበሽታ መከላከያና መቆጣጠርያ ማዕከል በኩል የአገራትን የጤና ስርዓት ለማጎልበት፣ ለባለሞያዎች ስልጠና ለመስጠት፣ የሕክምና መሳሪያዎችን ለመግዛት እና መሰል ድጋፎችን ለማድረግ ይውላል ብለዋል፡፡

በቡድን 7 አገራት አደረጃጀት በኩል እንደተገለጸው የአውሮፓ ሕብረት በዓለም አቀፍ ደረጃ የክትባትን ፍትሃዊ ተደራሽነት ለማረጋገጥ ለሚሰራውና ኮቫክስ ለተሰኘው ተቋም የሚያደርገውን ድጋፍ ከ500 ሚሊዮን ዩሮ ወደ 1 ቢሊየን በእጥፍ ማሳደጉንም ነው ፕሬዚዳንቷ የገለጹት፡፡

አያይዘውም አቅርቦቶችም በቅርቡ ይጀመራሉ ዓለም የሚተባበርበት እውነተኛ ጊዜ አሁን ነውም ብለዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version