Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአሜሪካ በኮሮና ህይዎታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 500 ሺህን አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአሜሪካ በኮሮና ሳቢያ ህይዎታቸው ያለፈ ሰዎች 500 ሺህን አልፏል፡፡

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ እስካሁን ከ500 ሺህ 70 በላይ ሰዎች ህይዎታቸው ሲያልፍ፤ ከ28 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

አገሪቱን በአለማችን ቫይረሱ ከጸናባቸው አገራት በቀዳሚነት ትጠቀሳለች፡፡

በዚህም በኮቪድ-19 ሳቢያ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎቿ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ምክትላቸው ካማላ ሀሪስ በተገኙበት የሻማ ማብራት ስነስርዓት እና የህሊና ጸሎት አድርገዋል፡፡

‘’እንደ ሀገር ቫይረሱ ያደረሰብን ሀዘን ልብ የሚሰብር ነው’’ ያሉት ፕሬዚዳንቱ ፤ ‘’ሁሉም አሜሪካውያን በሞት ያጣናቸውን ዜጎች በጸሎት ልናስባቸው ይገባል‘’ ብለዋል፡፡

በተጨማሪም አሜሪካውያን ከቫይረሱ ራሳቸውን እንዲጠብቁም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

እስካሁን በአለም ዙሪያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ112 ሚሊየን 279 ሺህ በላይ ሲሆን፤ ከ2 ሚሊየን 485 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በአንጻሩ ከ87 ሚሊየን 814 ሺህ በላይ ከቫይረሱ ሰዎች አገግመዋል፡፡

በዚህም ከአሜሪካ በመቀጠል ህንድ፣ ብራዚል፣ ሩሲያ እና ብሪታንያ ቫይረሱ ከጸናባቸው አገራት በቅድሚያ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ እና ዎርልድ ኦ ሜትር

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version