Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሰልጣኝ ዘማሪያም ወ/ጊዮርጊስ የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ዘማሪያም ወልደጊዮርጊስ የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ በመሆን በይፋ ክለቡን መረከባቸው ተነገረ፡፡
አሰልጣኙ ከዚህ በፊት የወልዋሎ አዲግራት እግር ኳስ ክለብን ጨምሮ አዳማ ከተማ፣ ፋሲል ከነማ፣ ወልድያ ከተማ እና ጅማ አባ ጅፋርን ማሰልጠናቸው ይታወሳል፡፡
አሁን ደግሞ በአንድ አመት ውል ድሬዳዋ ከተማን መቀላቀላቸው ታውቋል፡፡
ቡድኑን ወደተሻለ ደረጃ ማድረስም የቤት ስራቸው እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን ስራቸውን ደግሞ የፊታችን ሐሙስ ሐዋሳ ከተማን በመግጠም ይጀምራሉ መባሉን ከኢትዮኪክኦፍ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ድሬዳዋ ከተማ ከበፊቱ አሰልጣኝ ፍሰሃ ጥዑመልሳን ጋር መለያየታቸው ይታወሳል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version