Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቆቦ፣ በፍላቂት ገረገራ እና ወልድያ ከተሞች የለውጥ አመራሩን የሚደግፉ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሄዱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቆቦ፣ በፍላቂት ገረገራ እና ወልድያ ከተሞች የለውጥ አመራሩን የሚደግፉ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሄዱ፡፡

በሰልፉ አገራዊ ለውጡን የሚደግፍ እና ኢትዮጵያዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ መልዕክልቶች የተንጸባረቁ ሲሆን፤ ለለውጥ አመራሩ የሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡

የድጋፍ ሰልፉ የለውጥ አመራሩ እስካሁን ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ ሥራዎች ግምት ውስጥ በማስገባት የበለጠ ተጠናክሮ ለውጡን እንዲያስቀጥል ለማሳሰብ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ዛሬ በቆቦ፣ ፍላቂት ገረገራ እና ወልድያ ከተሞች በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ነዋሪዎች የተለያዩ መልዕክቶችን ይዘው የወጡ ሲሆን፤ ለውጡን የሚደግፉ መፈክሮች ማሰማታቸውን ከሰሜን ወሎ ዞን መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

Exit mobile version