Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አባቶቻችን በአድዋ ድል የሀገራችዉን ሉአላዊነት ለማስከበር የሠሩትን አኩሪ ታሪክ ወጣቱ በልማት ሊደግመው ይገባል – አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አባቶቻችን በአደዋ ድል የሀገራችዉን ሉአላዊነት ለማስከበር የሠሩትን አኩሪ ታሪክ ወጣቱ በልማት ሊደግመው ይገባል ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ተናገሩ፡፡
125ኛው የአደዋ ድል በአል በአፋር ክልል ደረጃ በሠመራ ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተከብሯል።
በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ “የአድዋ ድል የምንኮራበት ብቻ ሳይሆን ወቅታዊ ችግሮቻችንን እየፈታን እድነታችንንና ልማታችንን ልናስቀጥልበት የሚገባን እርሾ ነው” በማለት ገልጸዋል፡፡
ዛሬም ሀገራችን ከአድዋ ያልተናነሱ ታሪክ ለሚሠራበት የህዳሴ ግድብ ግንባታ እንቅፋት የሚሆኑ የውስጥና የውጭ ስጋቶችን በአንድነት በመጋፈጥ የአባቶችን አኩሪ ታሪክ በልማት መድገም እንደሚገባም አስገንዘበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version