Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በትግራይ ክልል እና በመተከል ዞን ለተጎዱ ዜጎች የሚውል 50 ሺህ ብር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በትግራይ ክልል እና በመተከል ዞን ለተጎዱ ዜጎች በግላቸው 50 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

“ሰብዓዊነትና ፍቅር ለትግራይና መተከል” በሚል የሚንቀሳቀሰው የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሊቀመንበር ታማኝ በየነ ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር ተወያይቷል።

ኮሚቴው ለኢትዮጵያውያን መብት ልዩ የእርዳታ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ሲያካሂድ መቆየቱ የሚታውስ ነው፡፡

ፕሬዚዳንቷም በዚሁ ጊዜ በግላቸው በትግራይ ክልል እና በመተከል ዞን ለተጎዱ ዜጎች የሚውል የ50 ሺህ ብር ድጋፍ አበርክተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በጥምረት እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ መልካም መሆኑን በመግለፅ ይህን መሰሉ የድጋፍ ጥረት ኢትዮጵያዊነትን ለማጠናከር ያለው ፋይዳ ትልቅ እንደሆነ ተናግረዋል።

እርሳቸውም ከጥምረቱ እንቅስቃሴዎች ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴው እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሲያካሂድ በነበረው ድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻ በርካቶች ሲሳተፉ ቆይተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version