አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዶክተር አርከበ ዕቁባይ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንዲወዳደሩ በሙሉ ድምጽ መምረጡን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አስታወቀ።
ህብረቱ ዶክተር አርከበ ብቸኛው አፍሪካዊ እጩ በማድረግ ማቅረቡን ነው በመግለጫው ያመለከተው።
የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት 38ኛ መደበኛ ስብሰባ በየካቲት 24 እና 25 2013 ባደረገበት ወቅት ኢትዮጵያን እና አፍሪካን ወክለው እንዲወዳደሩ ውሳኔ አሳልፏል።
ዶክተር አርከበ ባለፉት ሰላሳ አመታት ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማትና ቀጣይነት ላለው ሁሉን አቀፍ መዋቅራዊ ሽግግር የሚያግዙ ፖሊሲዎችን በማውጣትና በማስተግበር ስኬታማ እንደሆኑ ህብረቱ ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!