Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ አህመድ ሺዴ በኢትዮጵያ ከጅቡቲ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በኢትዮጵያ ከጅቡቲ አምባሳደር መሃመድ ኢድሪስ ፋራህ ጋር ተወያዩ ፡፡
በውይይታቸው በሁለቱ ሃገራት ኢኮኖሚያዊ ትብብር ላይ በስፋት መክረዋል ፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ ሃገራቱ በመሰረት ልማት፣ በንግድ እና የህዝብ ለህዝብ ትብብርን ጨምሮ ስትራቴጂካዊ አጋርነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
ጅቡቲ ለኢትዮጵያ የገቢ እና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴ ለምትሰጠው አገልግሎት አድንቀው፥ የኢትዮጵያ መንግስት ለኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ግንኙነቶች ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል ፡፡
አምባሳደር መሃመድ በበኩላቸው ለአፍሪካ ቀንድ ልማትና ደህንነት መረጋገጥ ከኢትዮጵያ ጋር ተቀራርበው መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version