Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በህንድ በአንድ ቀን ብቻ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች ኮቪድ19 ተገኘባቸው

FILE PHOTO: A healthcare worker collects a coronavirus disease (COVID-19) test swab sample from a man as others watch, at a temporary shelter for the homeless in New Delhi, India, March 31, 2021. REUTERS/Adnan Abidi/File Photo

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህንድ ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ በአንድ ቀን ብቻ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን አስታወቀች፡፡

ህንድ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎቿ በአንድ ቀን ሲያዙ ከአሜሪካ በመቀጠል ሁለተኛዋ ሃገር ሆናለች፡፡

በአንድ ቀን የተያዙት ዜጎቿ 103 ሺህ 558 መሆናቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከአሜሪካና ከብራዚል በመቀጠል ወረርሽኙ የከፋባት ሦስተኛዋ ሃገር መሆኗን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

እስካሁን በህንድ 12 ነጥብ 6 ሚሊየን ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 165 ሺህ 101 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በህንድ ከየትኛውም የዓለም ክፍል በከፋ ሁኔታ ወረርሽኙ አድማሱን እያሰፋ ይገኛል ተብሏል፡፡

የህንድ የንግድ ከተማ በሆነችው ሙምባይ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከተከሰተው የወረርሽኙ ስርጭት 55 በመቶውን ድርሻ ትወስዳለች ነው የተባለው፡፡

መሰረታዊ የሚባሉ የቫይረሱ መከላከያ መንገዶች በአግባቡ አለመተግበራቸው ምክንያት መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ህንድ እስካሁን 76 ሚሊየን ዜጎቿን የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ስትሰጥ 9 ነጥብ 5 ሚሊየን ለሚሆኑት ደግሞ ሁለተኛውን ዙር ክትባት ማዳረሷን ገልጻለች፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version