Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በምስራቅ ምስራቅ ሪጅን የአራተኛ ትውልድ (4 ጂ) ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በምስራቅ ምስራቅ
ሪጅን የአራተኛ ትውልድ (4 ጂ) ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ አገልግሎትን በይፋ አስጀመረ።
ጅግጅጋ፣ ጎዴ፣ ፊቅ፣ ደገሃቡር፣ ቀብሪ በያህ፣ ዋርዴር እና ቀብሪ ደሀር ደግሞ የ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ አገልግሎት የተጀመረባቸው ከተሞች ናቸው።
የኢትዮ ቴሌኮም ስራ አስኪያጅ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ወቅቱ ከቦታ ቦታ በመዘዋወር ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ እንዲሁም አካባቢው በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጡ አስቸጋሪ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ሆኖም የአራተኛ ትውልድ ኤል ቲ ኢ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የኩባንያው ሰራተኞች ላደረጉት ተጋድሎ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በሪጅኑ የኔትወርክ ሽፋን እና አቅምን ለማሳደግ የሚያስችሉ የኔትወርክ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች በመከናወን ላይ እንደሚገኙም ወይዘሪት ፍሬህይወት መግለፃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version