Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሶማሊያ ፓርላማ የፕሬዚዳንት መሀመድ ፎርማጆችን ስልጣን ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት አራዘመ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሊያ ፓርላማ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብስባ የፕሬዚዳንት መሀመድ ፎርማጆን ስልጣን ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ማራዘሙ ተገለፀ።
የፓርላማው አፈ ጉባኤ መሀመድ ሙርሳል ሼኪህ እንደገለፁት ሶማሊያ ለቀጥታ ምርጫ እስከምትዘጋጅ ድረስ የፕሬዚዳንት ፎርማጆ የስልጣን ዘመን በሁለት ዓመታት ተራዝሟል።
ፓርላማው ያቀረበው ሃሳብ በ149 ድጋፍ፣ በአንድ ተቃውሞ እና ሶስት ድምፀ ተዓቅቦ ተቀባይነት ማግኘቱን ሬውተርስ ዘግቧል።
ሶማሊያ ባለፉት ወራቶች ከምርጫ መካሄድ አለመካሄድ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መግባቷ የሚታወስ ነው።
ፕሬዚዳንት መሀመድ ፎርማጆም ውሳኔውን በደስታ መቀበላቸውን በመግለፅ ውሳኔው ከምርጫው ጋር ተያይዞ ያሉ አለመስማማቶችን ለመቅረፍ እንደሚያስችል መናገራቸውን ነው ዴይሊ ኔሽን የዘገበው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

Exit mobile version