Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኮቪድ19 ጥንቃቄ መስፈርቶችን ላሟሉ ሆቴሎች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሲዳማ ብሔራዊ ክልል የኮቪድ19 ጥንቃቄ መስፈርቶችን ላሟሉ ሆቴሎች የእውቅና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መሰጠቱን የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልል ውስጥ 22 በቁጥጥር ቡድኑ ክትትልና ድጋፍ ከተደረገላችው ባለኮከብ ሆቴሎች ውስጥ 21ዱ የኮቪድ19 የጥንቃቄ መስፈርቶችን በአገልግሎት አሰጣጣቸው ውስጥ ተግባራዊ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
በዚህም የተቀመጡትን ዝርዝር መስፈርቶች አሟልተው በመገኘታቸው የእውቅና ሰርተፊኬት ተሰጥቷቸዋል።
የእውቅና አሰጣጡ እና የግምገማ ሂደቱ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪስት አገልግሎቶች ብቃት ማረጋገጥና ደረጃ ምደባ ባለሙያዎች እና ከሲዳማ ክልል ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ የተሰራ ሲሆን ቀጣይነት ያለው እና ተሞክሮ የተወሰደበት እንደሆነ መገለፁን ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version