Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበርን አስመልክቶ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለሚከበረው 16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን መሪ እቅድ የመጀመሪያ ረቂቅ በበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴው ቀርቦ ውይይት ተካሄደ።
በውይይቱ በ15ኛው አመት የበአሉ አከባበር ወቅት የነበሩ የሕገመንግስትና የፌዴራሊዝም አስተምህሮና የማህበራዊ በጎ ፍቃድ አገልግሎቶች በመልካም ተሞክሮዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ነው የተገለፀው።
ከባለፈው አመት በዓል አከባበር መሻሻል ካለባቸው ሁነቶች መካከል ደግሞ የክልሎች በዓል አከባበር እንዲሁም የሚድያና የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ተብሏል።
በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚያተኩር አውደ ጥናትና የንግድና ባዛር ኤግዚቢሽን በቀጣዩ 16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር ወቅት ሊካተቱ የሚገባቸው ኩነቶች እንደሆኑም በመድረኩ ተገልጿል።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ በመድረኩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህና የክልል ምክር ቤት አፈጉባኤዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
Exit mobile version