Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አደንዛዥ ዕፅ ሲያጓጉዝ የነበረ ተሽከርካሪ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሻሻመኔ ወደ ሞያሌ አደንዛዥ ዕፅ ይዞ ሲጓጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ መያዙን የጌዴዖ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን ታምራት ምትኩ ተሽከርካሪው ትናንት ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ በጉዞ ላይ እንዳለ ነው የተያዘው፡፡

በጉዞው ላይ ለሽፋን የከብት መኖ ይዞ እንደነበረ ነው ዋና ሳጅን የገለጹት፡፡

ተሽከርካሪውን ለማስመለጥ ሌሎች ተሽከርካሪዎች መንገድ በመዝጋት ድጋፍ ቢያደርጉም ፖሊስ ባደረገው ክትትል ሊያዝ እንደበቃ ነው ያስረዱት፡፡

እስካሁን በህብረተሰቡ ጥቆማ በበጀት ዓመቱ አራት መኪና አደንዛዥ ዕጽ እንደተያዘ ያስታወሱት ዋና ሳጅን ታምራት ህብረተሰቡ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ማሳሰባቸውን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version