Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኒጀር በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት 16 ወታደሮች ተገደሉ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኒጀር በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት በጥቂቱ 16 ወታደሮች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ፡፡
በምዕራብ ታሆዋ ክልል በደረሰው ጥቃት ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ ስድስት ወታደሮች ቆስለዋል ነው የተባለው፡፡
ታጣቂዎቹ ከፈጸሙት ጥቃት በተጨማሪ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን መውሰዳቸውም ተነግሯል፡፡
ኒጀርን ከማሊ በሚያዋስናት ድንበር የሚገኘው የታሆዋ ክልል ከዚህ ቀደም በታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃት የሚፈጸምበት አካባቢ መሆኑ ይነገራል፡፡
አሁን ጥቃት የተፈጸመበት ቦታም ባለፈው መጋቢት ወር በተፈጸመ ጥቃት ከ200 በላይ ሰዎች ለህልፈት የተዳረጉበት ስፍራ ነው ተብሏል፡፡
ምንጭ ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version