Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ወደ ሱዳን አቀኑ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ወደ ሱዳን አቅንተዋል።

በፕሬዚዳንቱ በሚመራው ልዑክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦስማን ሳሌህ እና የፕሬዚዳንቱ አማካሪ የማነ ገብረአብ እንደሚገኙ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ፕሬዚዳንቱ በሱዳን በሚኖራቸው ቆይታ በተለያዩ ጉዳዮች ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚመክሩ ነው የተነገረው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version