Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ውጤታማ እና ተዓማኒ እንዲሆን የመገናኛ ብዙሃን ሚና የጎላ ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “የመገናኛ ብዙሃን ሚና በ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ” በሚል ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ወርቅነሽ ብሩ ኢትዮጵያ ዘንድሮ የምታካሂደው ምርጫ ተዓማኒ፣ ግልጽና ሰላማዊ እንዲሆን የመገናኛ ብዙሃን ከመቼውም ጊዜ በላይ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡
የመገናኛ ብዙሃን በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫና በድህረ ምርጫ ወቅት ሊያደርጓቸው ስለሚገቡ ጉዳዮች አንስተዋል።
በቅድመ ምርጫ ወቅትም የፖለቲካ ፓርቲዎች የያዛቸውን ፕሮግራሞችና ማኒፌስቶ በትክክል ወደ ህብረተሰቡ በማድረስ ህብረተሰቡ በትክክል እንዲወስን ሊያደርጉ ይገባል ነው ያሉት።
በምርጫ ወቅትም ህብረተሰቡ በዲሞክራሲያዊ መንገድ በነቂስ ወጥቶ እንዲመርጥ ብሎም በድህረ ምርጫ ወቅትም ትክክለኛ ውጤቱንና መረጃን በአግባቡ በመዘገብ ሃላፊነታቸውን መወጣት ይገባል ብለዋል።
በሃይማኖት ኢያሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version