Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጆሴ ሞውሪንሆ የሮማ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጆሴ ሞውሪንሆ የጣሊያኑ ሮማ አሰልጣኝ ሆነ መሾማቸው ተገለፀ።
በቅርቡ ከእንግሊዙ ቶተንሃም ጋር የተለያዩት ሞውሪንሆ የዘንድሮው የጣሊያን ሴሪያ አ ሲጠናቀቅ ከሮማ ጋር የሚለያዩትን ፓውሎ ፎንሴካን ይተካሉ ተብሏል።
የሀገራቸውን ልጅ ተክትው ወደ ጣሊያን የሚያመሩት ጆሴ ሞውሪንሆ ከፈረንጆቹ 2021 እስከ 2024 የውድድር ዘመን ሮማን እንደሚያሰለጥኑ ቢቢሲ ዘግቧል።
ሞውሪንሆ የሮማ አሰልጣኝ መሆናቸው ከተነገረ በኋላ በሰጡት አስተያየት የማይታመነው የሮማ ክለብ ደጋፊዎች ስሜት ሃላፊነቱን እንዲረከቡ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

Exit mobile version