Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የግንቦት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሚያዝያ ወር የነበረው የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ የግንቦት ወር የመሸጫ ዋጋ ሆኖ እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 30 ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ነው የተገለጸው።

የአውሮፕላን  የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የዓለም የነዳጅ ዋጋን መሰረት በማድረግ ተሰልቶ የተገኘው 11 ሣንቲም በመጨመር በሚያዚያ ወር ሲሸጥበት ከነበረው 43 ብር ከ70 ሳንቲም ወደ ብር 43 ብር ከ81 ሳንቲም ከፍ እንዲል መወሰኑን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version