Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በናይል ተፋሰስ አካባቢ ያለውን ኢንቨስትመንት ለማነቃቃት ታሳቢ ያደረገው 6ኛው የናይል ተፋሰስ ልማት ስብሰባ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በናይል ተፋሰስ አካባቢ ያለውን ኢንቨስትመንት ለማነቃቃት ታሳቢ ባደረገ መልኩ ሲካሄድ የቆየው 6ኛው የናይል ተፋሰስ ልማት ስብሰባ ተጠናቋል።
ስብሰባው የኮቪድ ስርጭትን ተከትሎ በበይነ መረብ አማካኝነት ሲካሄድ መቆየቱ ተመላክቷል።
የናይል ተፋሰስ ልማት ስብሰባ የመዝጊያ መርሀ ግብር ላይ የውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በዚሁ መድረክ ላይ የውሀ ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ÷ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው 6ኛው የናይል ተፋሰስ የልማት ስብሰባ የአካባቢ ጥበቃና ድንበር ተሻጋሪ የውሀ ሀብትን በጋራ መጠቀምና ማልማት ጨምሮ የአየር ንብረት ለውጥ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።
የናይል ተፋሰስ ሀገራት በተፈጥሮ ሀብት የጋራ ተጠቃሚነት ዙሪያ ላይ መግባባት እንዲኖር የሚያስችል ውይይት መደረጉንም ሚኒስትሩ አመላክተዋል።
በየሸዋ ማስረሻ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version