Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 398 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋቸሞ ዩኒቨርስቲ በሆሳዕና እና በዱራሜ ግቢዎች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 398 ተማሪዎች በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ አስመረቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 23ቱ በሁለተኛና ቀሪዎቹ በመጀመሪያ ዲግሪ የተሰጣቸውን ስልጠና ያጠናቀቁ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ ተከታታይ መርሀ ግብር በማህበራዊ ሳይንስ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በቴክኖሎጂና በግብርና ዘርፎች የሰለጠኑ ናቸው።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንተነህ ተስፋዬን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version